"... ፊደል ፤ (ኢሳ፳፱፡፲፩) መዠመሪያ ትምርት ተቀዳሚ ጥፈት። ከአልፍ እስከ ፐ ያለ ፴፯ ኅርመት ባለ፯ ቅንጣት። ከዚሁ ደግሞ እነጐኈኰቈ ባለ፭ ቅንጣት ናቸው። አበገደን ተመልከት። የፊደል ትርጓሜ የነገር የቃል ምልክት ሥዕል መጕሊያ መግለጫ ማለት ነው። መዝገበ ፊደል እይ። ፊደሎች ፤ (ፊደላት) ኹለትና ከኹለት በላይ ያሉ ብዙዎች። ፊደላዋሪያ ፤ (ፊደለ ሓዋርያ) ፤ ልጆች ከፊደል በኋላ የሚማሩት መዠመሪያው የዮሐንስ መልክት (፩ዮሐ፡፩--፯)። ፊደል መባሉ እንደ ፊደል ስለ ተጻፈ ነው። ..." አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት